የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን (ኢሰማኮ) የዓለም የሠራተኞችን ቀን (ሜይ ዴይ) አክብሯል፡፡
ኢሰማኮ በዓለም ለ136ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ ሚከበረውን የሠራተኞች ቀን በተለያዩ መርሃ ግብሮች ነው ያከበረው፡፡
በበዓሉ ላይ በኮንፌዴሬሽኑ ስር የሚገኙ የሠራተኛ ፌዴሬሽኖችና የማህበራት ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡
በመድረኩ ፌዴሬሽኖቹ ከኮንፌዴሬሽኑ ጋር በጋራ በሚሠሩባቸውና የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ላይ አጋርነታቸውን አሳይተዋል።
የሰራተኞች በዓል በኢትዮጵያ ከሚያዚያ 23/1968 ዓ.ም ጀምሮ ህዝባዊ በዓል ሆኖ እየተከበረ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡
በበዓሉ ላይ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዳንኤል ተሬሳን፣ የኮንፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
በአንዋር አሕመድ