ዩክሬን ላይ ኒውክሌር ለመጠቀም የሚያስገድድ ሁኔታ እንደማይኖር “ተስፋ አደርጋለሁ” – ፑቲን

You are currently viewing ዩክሬን ላይ ኒውክሌር ለመጠቀም የሚያስገድድ ሁኔታ እንደማይኖር “ተስፋ አደርጋለሁ” – ፑቲን

AMN ሚያዝያ 27/2017

ዩክሬን ላይ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ለመጠቀም የሚያስገድድ ሁኔታ እንደማይኖር “ተስፋ አደርጋለሁ” ሲሉ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተናግረዋል።

ፑቲን ይህን የተናገሩት የእርሳቸውን የሩብ ምዕተ ዓመት ሀገር የመምራት ጉዞ አስመልክቶ ትናንት በሩሲያ ብሔራዊ የቴሌቭዥን ጣቢያ በተላላፈ ዘጋቢ ፊልም ላይ ነው።

ፕሬዚዳንቱ ዩክሬይን በሩሲያ ላይ ስለምትፈጽመው ጥቃት ተጠይቀው ሲመልሱ ፤ “በጦርነቱ እስካሁን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ መጠቀም አላስፈለገንም….ወደፊትም ለመጠቀም እንደማንገደድ ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል።

ፑቲን ሰለኒውክሌር የሰጡት ሐሳብ ፤ ቀድሞውኑ “አልበላሽምን ምን አመጣው!” በሚለው ብሂል መሰረት በኪየቭ የሰላም ዝግጁነት ላይ የቀይ መብራት ምልክት ተደርጎ እንዳይቆጠር ስጋት ፈጥሯል።

ቭላድሚር ፑቲን ሀገራቸው እ.አ.አ በ2022 ከዩክሬን ጋር ለገባችበት ጦርነት “አሳማኝ እና ለሩሲያ ተስማሚ” ፍፃሜ ለማስገኘት “ጥንካሬ እና ብልሃት” እንዳላት ማስታወቃቸውንም አል ጃዚራ ዘግቧል።

ሩሲያ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከአጋሮቿ ጋር በመሆን በናዚ ጀርመን ላይ ድል የተቀዳጀችበትን 80ኛ ዓመት አስመልክቶ ከፈረንጆቹ ግንቦት 8 እስከ 10 የሚቆይ የሦስት ቀናት የተኩስ አቁም ማወጇ ይታወቃል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review