ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ልዑክ ጋር በመሆን ለስራ ጉብኝት ዛሬ ፈረንሳይ ፓሪስ ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓሪስ ሲደርሱ በብሔራዊው የጦር ኃይሎች ሙዚየም የአቀባበል ሥነሥርዓት የተደረገላቸው ሲሆን፣ በጉብኝታቸው ከፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተገናኝተው የሚወያዩ እንደሚሆን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።