ዘንድሮ 23 ሚሊዮን ዜጎች ከተረጂነት መላቀቃቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ

You are currently viewing ዘንድሮ 23 ሚሊዮን ዜጎች ከተረጂነት መላቀቃቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ

AMN- ሰኔ 276/2017 ዓ.ም

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 42ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው በ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡

በማብራሪያቸውም የማንሰራራት ዓመት ብለን በጀመርነው ዓመት ታይቶ የማይታወቁ ድሎችን የተጎናጸፍንበት ነዉ ብለዋል፡፡

በዓመቱ ለተጎናጸፍናቸው ድሎች የኢትዮጵያ ህዝብና የምክር ቤት አባላት ለነበራቸው ሚና ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ 27 ሚሊዮን ተረጂዎች እንደነበሩ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እነዚህን ዜጎች ደረጃ በደረጃ ከሴፍቲኔት ነፃ ለማውጣት በትኩረት በመሠራቱ ውጤት መጥቷል ብለዋል፡፡

የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋጋጥ ቀሪ ከ4 ሚሊዮን ያነሰ ተረጂ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከተረጂነት ለማላቀቅ እንደሚሰራም አስታውቀዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review