ኢትዮጵያ ከተቀረው ዓለም ጋር ያላትን የዲፕሎማሲ ሚዛን ጠብቃ እንደምትጓዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ

You are currently viewing ኢትዮጵያ ከተቀረው ዓለም ጋር ያላትን የዲፕሎማሲ ሚዛን ጠብቃ እንደምትጓዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ

AMN- ሰኔ 26/2017 ዓ.ም

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 42ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ኢ-ተገማች በሆነው የገሀዱ ዓለም ነባራዊ ሁኔታም፣ እንደ ሀገር ብሄራዊ ጥቅማችንን ባስጠበቀ መልኩ መጓዝ ይጠይቃል ብለዋል፡፡

ወቅታዊ የዓለም ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት አማካኝ የሆነውን መንገድ ይዞ መጓዝ ወቅቱ የሚሻው ጉዳይ እንደመሆኑ፣ ወዳጆቻችንን ጠበቅ የማይወዱንንም አለዝበን ማለፍ አለብን ሲሉም አብራርተዋል፡፡

ጎረቤት ሀገራትን በተመለከተ በሰጡትም ማብራሪያም፣ አንዳችን ለአንዳችን በጣም እናስፈልጋለን፤ነገር ግን በንግድና በድንበር ያደሩና ያልተፈቱ ጉዳዮች ዲፕሎማሲያችን ላይ ወጣ ገባ እንዲኖር በር ከፍቷል ብለዋል፡፡

ልክ እንደ ግሪን ሌጋሲው በእኛ በኩል መልካም ዘርን እየዘራን እንሄዳለን፣ ቀይ ባህርም ላይ ያለን አመለካከትም ይሄው ነው ብለዋል፡፡

የኤርትራ ሉአላዊነትን እያከበርን ሉአላዊት የሆነችው ኢትዮጵያም የባህር በር እንዲኖራት በሰጥቶ መቀበል መርህ በንግግር መፍትሄ ማግኘት ይኖርበታል በማለትም ገልጸዋል፡፡

በኤርትራ በኩል ውጊያ እንደሚነሳ የሚነዛው ጉዳይ በተመለከተም፣ ተባበረን በሰላምና በንግግር ማደግ ብቻ ነው የምንፈልገው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ላላፉት ሰባት ዓመታት ከየትኛውም ጎረቤት ሀገር ጋር ጦርነት ውስጥ አልገባችም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ነገር ግን በሰላም የማያኖር ነገር ካለ እራሳችንን ለመከላከል በቂ አቅም አለን ብለዋል፡፡

በሚካኤል ህሩይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review