እንጦጦ ላይ ያሉ ባህር ዛፎች ሙሉ በሙሉ እንደሚነሱ ተገለጸ

You are currently viewing እንጦጦ ላይ ያሉ ባህር ዛፎች ሙሉ በሙሉ እንደሚነሱ ተገለጸ

AMN- ሰኔ 27/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ተራራማ ቦታ በእንጦጦ ላይ የሚገኙት ባህር ዛፎች በቀጣይ ሦስት ዓመታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ እንደሚነሱ እና በሀገር በቀል ዛፎች እንደሚተኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግርማ ሰይፉ ገለጹ።

ቢሮ ኃላፊው ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ኤፍ ኤም 96.3 ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ባህር ዛፍ ውሃ የመምጠጥ አቅሙ ከፍተኛ በመሆኑ መዲናዋ የከርሰ ምድር ውሃን በአግባቡ እንዳትጠቀም ማድረጉን ነው ያብራሩት።

አቶ ግርማ በማብራሪያቸው፣ ባህር ዛፎቹ ሲነሱ ግን በእጥፍ በሀገር በቀል ዛፎች እና ስነ ምህዳሩን ለማስተካከል በሚችሉ ዛፎች እየተተኩ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ከተጀመረ ወዲህ ከእንጦጦ ተነስተው ወዳ መሀል ከተማ የሚፈሱት ወንዞች የውሃ መጠን መጨመሩንም ነው ኃላፊው ያነሱት፡፡

በሲሳይ ንብረቱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review