አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እና የከተማው የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸዉን ስምምነት ተፈራረሙ

You are currently viewing አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እና የከተማው የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸዉን ስምምነት ተፈራረሙ

AMN- ሐምሌ 3/2017 ዓ.ም

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እና የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ “ቤት አዲስ” የተሰኘ ሳምንታዊ የቴሌቪዥን ፕሮግራም በጋራ ለመስራት ስምምነት አድርገዋል::

በመርሐ-ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቅድስት ወልደጊዮርጊስ፣ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የከተማዋ የጀርባ አጥንት ሚዲያ እየሆነ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ቢሮው የተለያዩ የቤት ልማት አማራጮችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀው፣ እያከናወናቸው ያሉ ስራዎችን ለማስተዋወቅ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክን ተመራጭ ሚዲያ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

በእስካሁኑ ሂደትም ቢሮው ለሰራቸው ስራዎች ኤ ኤም ኤን አሻራውን ማሳረፉንም ጠቁመዋል።

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ፣ የትውልድ ድምፅ የሆነው አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ተደራሽ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸው፣ ተቋሙን ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ እየሰራቸው ያሉ ስራዎችን ለህብረተሰቡ መረጃ በመስጠት እና ክፍተቶችን በመለየት በትብብር ይሰራልም ብለዋል፡፡

ተቋሙ በቴክኖሎጂ በአደረጃጃት እና በይዘት ሪፎርም እያደረገ እንደሚገኝም ተናግረዋል::

ውል የተገባበት “ቤት አዲስ” የተሰኘው የቴሌቪዥን ፕሮግየራም በየሳምንቱ የሚተላለፍ ሲሆን፣ የ15 ደቂቃ ፍጆታም ይይዛል፡፡

በቴዎድሮስ ይሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review