የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ሞንዴይ ሰማያ ኩምባ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ዘሪሁን አበበ እና ሌሎች የሚኒስቴሩ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ሞንዴይ ሰማያ ኩምባ በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።