ገዳ ባንክ በተጠናቀቀዉ የበጀት ዓመት ዉጤታማ ስራዎችን ማከናወኑን ገልጿል፡፡
የገዳ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ቡልቶ ገዳ ባንክ ወደ ኢንዱስትሪው ከገባ አጭር ጊዜ ቢሆነውም በበጀት ዓመቱ ስኬታማ ለውጥ እያስመዘገበና በባንክ ኢንዱስትሪው ተወዳዳሪ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል።
ባንኩ አገልግሎቱ ለማስፋት ከተለያዩ ሀገራት ጋር ሲሰራ መቆየቱን ዋና ስራ አስፈፃሚው አያይዘው ገልፀዋል።
አገልግሎቱን በማዘመንና ዲጅታላይዝ በማድረግም ለደንበኞች ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት መቻሉንም አብራርተዋል።
ባንኩ በተለያዩ የሃሪቱ ክፍሎች ከመቶ በላይ ቅርንጫፎችን በማስፋፋት የተለያዩ የባንክ አገልግሎቶች በመስጠት ላይ እንደሚገኝም ጨምረዉ ገልጸዋል፡፡
በፂዮን ማሞ