በባንግላዴሽ በትምህርት ተቋም ላይ የአየር ኃይል ጀት ተከስክሶ በትንሹ የ19 ሰዎች ህይወት አለፈ

You are currently viewing በባንግላዴሽ በትምህርት ተቋም ላይ የአየር ኃይል ጀት ተከስክሶ በትንሹ የ19 ሰዎች ህይወት አለፈ

AMN- ሐምሌ 14/2017 ዓ.ም

በልምምድ ላይ የነበረ የባንግላዴሽ አየር ኃይል ጀት በሀገሪቱ ዋና ከተማ ዳካ በሚገኝ የትምህርት ተቋም ላይ ተከስክሶ የ19 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 164 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

ልምምድ ላይ የነበረው ኤፍ-7 ጀት በደረሰበት ብልሽት ምክንያት መከስከሱን የሀገሪቱ የጦር ኃይል አስታውቋል።

የጀቱ አብራሪም ከሟቾቹ መካከል አንዱ እንደሆነና፣ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ከ50 በላይ ህፃናት እና አዋቂዎችም ለህክምና እርዳታ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተዘግቧል።

አደጋው የደረሰበት የትምህርት ተቋም ከ4 እስከ 18 ዓመት እድሜ ያላቸው ተማሪዎች የሚማሩበት እንደሆነ ቢቢሲ ዘግቧል።

የነፍስ አድን ሰራተኞች በስፍራው ርብርብ እያደረጉ እንደሚገኝም ተመላክቷል።

የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት ጠንካራ ምርመራ፤ እንዲሁም በአደጋው ለተጎዱ ድጋፍ እንደሚደረግ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል።

ሀገሪቷም በነገው ዕለት ብሔራዊ የሀዘን ቀን ማወጇ ተዘግቧል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review