ሩሲያ እና ዩክሬን የጦር እስረኞችን ለመለዋወጥ ተስማሙ

You are currently viewing ሩሲያ እና ዩክሬን የጦር እስረኞችን ለመለዋወጥ ተስማሙ

AMN-ሐምሌ 17/2017 ዓ.ም

ሩሲያ እና ዩክሬን በኢስታንቡል ባደረጉት ሶስተኛው ዙር ውይይት እያንዳንዳቸው 1ሺህ200 የጦር እስረኞችን ለመለዋወጥ መስማማታቸውን አንድ የሩሲያ ተደራዳሪ መናገሩን አር ቲ ኢ ዘግቧል።

ተደራዳሪው አክለውም ሞስኮ በጦርነቱ የሞቱ የ 3ሺህወታደሮችን አስከሬን ለኪየቭ አሳልፋ እንደምትሰጥም አሳውቋል።

የጦር እስረኞችን መለዋወጥ እንደሚቀጥሉ እና፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ቢያንስ 1ሺህ200 ተጨማሪ የጦር እስረኞችን ከሁለቱም ወገኖች እንደሚለዋወጡ ተስማምተናል ብለዋል።

ጦርነቱን ለማስቆም የዩክሬን እና የሩሲያ አቋሞች አሁንም በጣም የተራራቁ ናቸው ብለዋል።

በድርድሩ ላይ በስፋት መወያየታቸውን እና ግንኙነታችንን ለመቀጠል ተስማምተናል ሲሉ ሜዲንስኪ ለአር ቲ ኢ ጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ሁለቱም ወገኖች የሞቱትን ወታደሮች እና የቆሰሉትን ለመለዋወጥ ፤ ሩሲያ ከ24 ሰአት እስከ 48 ሰዓታት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት ለዩክሬን መስጠቷንም ሜዲንስኪ አክለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዩክሬን ወገን አንድ ተደራዳሪ ከነሀሴ ወር መጨረሻ በፊት ፤ በዩክሬኑ ፕሬዝዳንት እና በሩሲያው ፕሬዝዳንት መካከል የውይይት ሀሳብ ቀርቦ የነበረ መሆኑን ተናግረዋል።

በዩክሬን እና በሩሲያ ባለስልጣናት መካከል የተደረገው የሶስተኛው ዙር የሰላም ድርድር ፤ አሜሪካ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ግፊት በተደረገበት ወቅት የተደረገ ነው ተብሏል።

በየካቲት 2022 የተከፈተው የሩስያ – ዩክሬን ጦርነት የምስራቅ እና የደቡብ ዩክሬን ግዛቶችን ማውደሙን እና በአስር ሺዎች ለሚቆጠሩ ወታደሮች እና ንፁሀን ዜጎች ሞት ምክንያት መሆኑን አር ቲ ኢ ዘግቧል።

በብርሃኑ ወርቅነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review