በብዛትና በጥራት የተገነቡት የስፖርት ማዘውተሪያዎች ለስፖርቱ ቤተሰብ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ ተገለፀ

You are currently viewing በብዛትና በጥራት የተገነቡት የስፖርት ማዘውተሪያዎች ለስፖርቱ ቤተሰብ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ ተገለፀ

AMN – ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም

የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በብዛትና በጥራት በመሰራታቸው ለስፖርት ወዳዱ ቤተሰብ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን እንዳሉት፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን በማስፋፋት በአዕምሮ የበለጸገና ጤናው የተጠበቀ፣ የነገዋን ኢትዮጵያ የሚረከብ ትውልድ ለማፍራት በክረምቱ ውድድሮችን በማመቻቸት በሁሉም ክፍለ ከተሞች በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ከተማ አስተዳደሩ የወጣቶቹን ጥያቄ ለመመለስ የማዘውተሪያ ስፍራዎችን በአጭር ጊዜ፣ በፍጥነት እና በጥራት አጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት በማድረጉ ወጣቶችና ተማሪዎች የእረፍት ጊዜያቸውን በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እንዲያሳልፉ ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥሯ ብለዋል፡፡

በአምስት የስፖርት ስልጠና ማዕከላት፣ በ23 የስፖርት ዓይነቶች ከ60ሺ በላይ ታዳጊዎች እየሰለጠኑ እና ውድድሮችንም እያካሄዱ እንደሚገኙ ተገልጿል።

በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች የታዳጊ ወጣቶች ስልጠናና ፕሮጀክቶችን ጨምሮ ጤና ቡድችም በንቃት እየተሳፉ ይገኛል ብለዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ 122 ሜዳዎችን ጨምሮ ከለውጡ ወዲህ 1500 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውንም ሀለፊው ተናግረዋል።

በአለኸኝ አዘነ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review