የናይጄሪያ መንግሥት የኢትዮጵያን አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በመደገፍ 2ሺህ የናይጄሪያ ካሹ ችግኝ እና 100 ሺህ የካሹ ዕጽዋት ዘር አበረከተ

You are currently viewing የናይጄሪያ መንግሥት የኢትዮጵያን አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በመደገፍ 2ሺህ የናይጄሪያ ካሹ ችግኝ እና 100 ሺህ የካሹ ዕጽዋት ዘር አበረከተ

AMN – ሐምሌ 20 ቀን 2017

የናይጄሪያ መንግሥት የኢትዮጵያን አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በመደገፍ 2ሺህ የናይጄሪያ ካሹ ችግኝ እና 100 ሺህ የካሹ ዕጽዋት ዘር አበርክቷል።

ከናይጄሪያ መንግሥት የተላከው ችግኝ እና ዘር ቦሌ በዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ካርጎ በመገኘት በኢትዮጵያ የናይጄሪያ አምባሳደር ናስር አሚኑ እና የናይጄሪያ ዋና የዕጽዋት ሳይንቲስት ዶ/ር ኢብራሒም ዶባ ለግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኢፋ ሙለታ እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳ/ጄ አምባሳደር ዘሪሁን አበበ አስረክበዋል።

አምባሳደር ዘሪሁን አበበ ይህ የናይጄሪያ መንግሥት የችግኝ እና ዘር ስጦታ የሁለቱን አገራት ግንኙነት በማጠናከር ረገድ ተምሳሌታዊ አንድምታ ያለው ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)በኢትዮጵያ የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር መክፈቻ ስነ ሥርዓት ላይ ለታደሙት የናይጄሪያው ምክትል ፕሬዝዳንት 4ሺህ ችግኞችን በሥጦታ መላካቸው ይታወሳል።

በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለው አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አሁን ላይ የበርካታ አገራትን ትኩረት እና እውቅናን እያገኘ በመሄድ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review