የብልጽግና ፓርቲ አመራሮችና አባላት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አካሄዱ

You are currently viewing የብልጽግና ፓርቲ አመራሮችና አባላት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አካሄዱ

AMN ሃምሌ 21/2017

በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች እና የብልጽግና ፓርቲ አባላት የተሳተፉበት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በሁሉም ክፍለ ከተሞች እየተካሄደ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ያስጀመሩት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በመዲናዋ አረንጓዴ ልማትን ማስፋፋቱ ይህም አንድ ከተማ ማሟላት ያለባትን ዓለም አቀፍ መስፈርት ለማሟላት ምቹ መደላድል የሚፈጥር መሆኑ በመርሃ ግብሩ ተገልጿል፡፡

የኮሪደር ልማቱም ለአረንጓዴ ልማት መርሃ ግብር መፋጠን ጉልህ ድርሻ ያበረከተ መሆኑና በጋራ በመትከል ከተማዋ አረንጓዴ እንድትለብስ እያስቻለ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

ከብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ እንደሚያመላክተዉ የብልፅግና ፓርቲ እሳቤ የሆነው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ይበልጥ እንዲተገበር የከተማዋ አባላት እና አመራሮች በነቂስ በመውጣት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review