ለወዳጅነት ጨዋታ ወደ ዩናይትድ ስቴት አሜሪካ ያቀናው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዲ ሲ ዩናይትድን 3ለ0 አሸነፈ ።
ለዋልያዎቹ ከነአን ማርክነህ ፣ ዳዋ ሆቴሳ እና ረመዳን የሱፍ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል ።
ዋሺንግተን በሚገኘው ኦውዲ ፊልድ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ባለሜዳው ዲ ሲ ዩናይትድ ከስድስት በላይ የአካዳሚ ተጫዋቾችን ተጠቅሟል ።
ሙሉ ወጪያቸው ተሸፍኖ ወደ አማሪካ ያቀኑት የቡሔራዊ ቡድኑ አባላት 20 ሺ ዶላር ይበረከትላቸዋል ።
ጨዋታውን በድል በመወጣታቸው ደግሞ ቃል የተገባላቸው የ50ሺ ዶላር ጉርሻ የሚሰጣቸው ይሆናል ።
በሸዋንግዛው ግርማ