በህንድ በጣለ ከባድ ዝናብ የ46 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 200 የሚሆኑ ያሉበት አልታወቀም

You are currently viewing በህንድ በጣለ ከባድ ዝናብ የ46 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 200 የሚሆኑ ያሉበት አልታወቀም

AMN – ነሐሴ 9/2017 ዓ.ም

በህንድ ካሽሚር ክልል ተራራማዋ ስሪናጋር ከተማ በጣለ ከባድ ዝናብ እና የጭቃ ናዳ የ46 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 200 የሚሆኑ የደረሱበት እንዳልታወቀ የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

ይህም ከሳምንት በጥቂት ቀናት በበለጠ ጊዜ ውስጥ በሂማላያስ የደረሰ ሁለተኛው ተፈጥሮአዊ አደጋ ያደርገዋል።

በአካባቢው የሚታወቅ ሃይማኖታዊ ጉዞ እየተደረገ ባለበት ወቅት የደረሰው የጎርፍ አደጋው የተጓዦች ማረፊያ ስፍራን፣ የማህበረሰብ ምግብ ማብሰያ እና የፍተሻ ስፍራን ጠራርጎ መውሰዱን ሮይተርስ ዘግቧል።

ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተጓዥ የምሳ እረፍት በሚያደርግበት ሰዓት አደጋው መድረሱንም ባለስልጣናቱ ተናግረዋል።

የአካባቢው ፖሊሶች እና የአደጋ ምላሽ ሰራተኞች ከስፍራው በመድረስ የጠፉ ሰዎችን በመፈለግና እርዳታ በመስጠት ርብርብ ላይ መሆናቸው ተነግሯል።

የከተማዋ የአየር ትንበያ ቢሮ አደጋው የደረሰበትን ስፍራ ጨምሮ በበርካታ የክልሉ ክፍሎች የጎርፍ እና የጭቃ ናዳ አደጋዎችን የሚያስከትል ከባድ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል አስጠንቅቆ እንደነበር ዘገባው አመላክቷል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review