ዲያዝ የመጀመሪያ ግቡን ባስቆጠረበት ጨዋታ ባየርን ሙኒክ የጀርመን ሱፐር ካፕ አሸናፊ ሆነ

You are currently viewing ዲያዝ የመጀመሪያ ግቡን ባስቆጠረበት ጨዋታ ባየርን ሙኒክ የጀርመን ሱፐር ካፕ አሸናፊ ሆነ

AMN – ነሃሴ 11/2017 ዓ.ም

የቡንደስሊጋ አሸናፊ ባየርን ሙኒክ ስቱትጋርትን በመርታት የጀርመን ሱፐር ካፕ አሸናፊ ሆኗል ።

ሙኒክ ጨዋታውን 2ለ1 ሲያሸንፍ ሀሪ ኬን እና ሊውስ ዲያዝ ግቦቹን በስማቸው አስመዝግበዋ።

ከሊቨርፑል ባየርን ሙኒክን የተቀላቀለው ዲያዝ ለጀርመኑ ክለብ የመጀመሪያ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

ለስቱትጋርት ጄሚ ሌውሊንግ ለውጥ ያልፈጠረችውን ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል።

ባየርን ሙኒክ የጀርመን ሱፐር ካፕን 11 ጊዜ በማንሳት ቀዳሚው ክለብ ሆኗል ። ከሙኒክ በመቀጠል ቦሩሲያ ዶርትመንድ ስድስት ጊዜ ዋንጫውን አንስቷል ።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review