አስራ አንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት መሠረቱ

You are currently viewing አስራ አንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት መሠረቱ

AMN ነሐሴ 14/2017

አስራ አንድ ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት መመስረታቸውን አስታወቁ።

ጥምረት የመሠረቱ የፖለቲካ ፓርቲዎችም በዛሬው ዕለት የምስረታ ጉባኤያቸውን በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።

በዚህም የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ልዩነቶቻቸውን በማክበር ለጋራ ዓላማ ተጣምረው እንደሚሰሩም ተጠቁሟል።

የጥምረቱ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዳሮት ጉምአ እንዳሉትም፤ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በጋራ መሰባሰብ አንድነት ሃይል መሆኑን በተግባር ያሳያል ብለዋል።

ፓርቲዎቹ የየራሳቸውን ዓላማ በመያዝ ለጋራ ስኬት ጥምረት መፍጠራቸው ጠቁመው፤ የተሻለ የፖለቲካ ባህልን ለመገንባት ትልቅ ሚና የሚጫወት መሆኑንም ተናግረዋል።

የፖለቲካ ፖርቲዎቹ መጣመር የተሻለች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስተላለፍ እንደሚጠቅም ጠቁመው፤ ለፖለቲካ ባህል መዘመንም የበኩሉን እንደሚወጣም ተናግረዋል።

የመተሣሠብ እና የመተባበር ዕድል የሚፈጠር እንዲሁም የሐሳብ ፖለቲካን ማንገስ ሌላኛው የጥምረቱ ዓላማ መሆኑንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ሃይሉ በዚሁ ወቅት፤ አቅምን በማሰባሰብ ለጋራ እና ለተሻለ ዓላማ መሥራት መልካም መሆኑን ተናግረዋል።

ልዩነቶችን በማክበር በጋራ መንቀሳቀስ ለጤናማ የፖለቲካ ስርዓት መዳበር ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑንም ገልጸዋል።

ጥምረቱ መጪው ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ተዓማኒ እንዲሆን የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀው፤ ቦርዱ ጥምረቱን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሰለሞን አየለ በበኩላቸው፤ የፓርቲዎቹ ጥምረት ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ መጎልበት ትልቅ ሚና ያለው መሆኑን ገልጸዋል።

ለመድብለ ፓርቲ ስርዓት ግንባታም ትልቅ ሚና ያለው መሆኑን ጠቁመው፤ ጥምረቱ ዘላቂ ሰላምን ለመፍጠር እና ለሀገራዊ መግባባት ስኬታማነት የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ መጠቆማቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ጥምር ፓርቲ የመሰረቱት አገው ለፍትሕና ዴሞክራሲ፣አገው ብሔራዊ ሸንጎ፣ ትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የዶንጋ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ ሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ አርጎባ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ አፋር ነፃ አውጭ ግንባር ፓርቲ፣ ከጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣የካፋ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ ካፋ አረንጓዴ ፓርቲ እና የጋምቤላ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ናቸው፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review