የመደመር መንግስት ዋና ግብ ኢትዮጵያን ለኢትዮጵያዊያን ማስረከብ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ

You are currently viewing የመደመር መንግስት ዋና ግብ ኢትዮጵያን ለኢትዮጵያዊያን ማስረከብ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ

AMN-ነሀሴ 14/2017 ዓ.ም

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር መንግስት በሚል በፃፉት አዲሱ መፅሀፍ ዙሪያ በሰጡት ማብራሪያ ላይ የመደመር መንግስት ዋና ግብ ኢትዮጵያን ለኢትዮጵያዊያን ማስረከብ ነው ብለዋል ።

የመደመር መንግስት ከሌላው የሚለየውም በውጤቱ እና በሂደቱ መሆኑንም ገልጸዋል ።

የሁሉም መንግስታት ርዕዮት በጥቅሉ ግዙፍ ኢኮኖሚን መገንባት እና የሀገራትን ደረጃ ማሻሻል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የመደመር መንግስት ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግቡ ግን ኢትዮጵያን ለኢትዮጵያውን ማስረከብ መሆኑን አብራርተዋል።

የመደመር መንግስት ኢትዮጵያን ለውስን ቡድኖች እና ግለሰቦች አይሰጥም ያሉ ሲሆን ለዚህም ሁለንተናዊ ብልፅግና ማረጋገጥ ላይ በማተኮር እየሰራ ነው።

ይህን ለመፈፀም ታዲያ የመደመር መንግስት አቋምና አቅም መደመር አለባቸው ብሎ ያምናልም ነው ያሉት።

ሚዛንና ፉክክርን መጠበቅም ሌላኛው ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል።

አቅምና አቋም ካልተደመሩ ጥቂቶች ዋና ብዙሀን እንደ 2ኛ ዜጋ የሚታዩበት እና የሀገር ባለቤትነት ጥያቄንም የሚያነሳ ይሆናል ብለዋል።

እያንዳዱ ዜጋ በፖለቲካውም ሆነ በሌሎች መስኮች እኩል የሚሳተፍበት አውድ ከሌለ አቅምና አቋም እንደማይደመሩ አስገንዝበዋል።

በኢትዮጵያም ዋናና አጋር የሚል አካሄድ እንደነበር አስታውሰው አሁን ግን በአካታችነት መተካቱን ተናግረዋል።

ይህም በኢትዮጵያ ለተመዘገበው ምርትና ምርታማነት ትልቅ አስተዋፅዖ አበርክቷል ብለዋል።

በማሬ ቃጦ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review