የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአሸንዳ ፣ አሸንድዬ፣ ሻደይ እና ሶለል በዓላት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ አሸንዳ፣ አሸንድዬ፣ ሻደይ እና ሶለል በክረምት ወራት በልጃገረዶች ከሚከበሩ የአብሮነት ክብረ በዓላት መካከል ናቸው ብለዋል።
ልጃገረዶች በተለያዩ ባህላዊ አልባሳት አምረው፣ በባህላዊ የፀጉር አሰራር ደምቀው እና ተውበው በነፃነት አደባባይ ወጥተው ባህልና አብሮነታቸውን ሲያሳዩ መመልከት እጅግ አስደሳች እንደሆነም ገልጸዋል።
እነዚህ በአላት በቀጣይም የበለጠ እሴታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ መጠበቅና መንከባከብ ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል።