ኮሎምቢያ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ከፈተች

You are currently viewing ኮሎምቢያ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ከፈተች

AMN – ነሐሴ 21/2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት የኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዝዳንት ፍራንሲያ ማርኬዝ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) በተገኙበት ኮሎምቢያ ኤምባሲዋን በአዲስ አበባ ከፍታለች ።

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፤ የኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዝዳንት ፍራንሲያ ማርኬዝ የኢትዮጵያ እና ኮሎምቢያ የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ያሳዩትን ቁርጠኝነት አድንቀዋል።

ይህም የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር እና ዲፕሎማሲያዊ ትብብርን ለማጎልበት ትልቅ እርምጃ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ፍራንሲያ ማርኬዝ ከሁለት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ አድርገውት በነበረው የስራ ጉብኝት ኮሎምቢያ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ለመክፈት መዘጋጀቷን ገልጸው ነበር።

ኢትዮጵያ እና ኮሎምቢያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩት እ.ኤ.አ በ1947 መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review