የኢትዮጵያን ይግዙ የንግድ ሳምንት ኤክስፖ ከነሀሴ 24 ጀምሮ ለ5 ቀናት ሊካሄድ ነው

You are currently viewing የኢትዮጵያን ይግዙ የንግድ ሳምንት ኤክስፖ ከነሀሴ 24 ጀምሮ ለ5 ቀናት ሊካሄድ ነው

AMN – ነሐሴ 21/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያን ይግዙ የንግድ ሳምንት ኤክስፖ ከነሀሴ 24 እስከ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ ሊካሄድ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

2ኛው የኢትዮጵያን ይግዙ የንግድ ሳምንት ኤክስፖ ከነሀሴ ከ24 ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት በመገናኛ የጥራት መንደር ሊካሄድ መሆኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

መግለጫውን የሰጡት የሚኒስቴሩ ሚንስትር ዴኤታ አብዱልሀኪም ሙሉ (ዶ/ር) ኤክስፖው ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነትን የሚያረጋግጥና የውጭ የኢኮኖሚ ተጋላጭነትን የሚቀንስ ስለመሆኑም ተናግረዋል።

ኤክስፖው የኢትዮጵያን ምርትና አገልግሎት የማስተዋወቅና የማበረታታት ሚናው የላቀ ስለመሆኑም ሚኒስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል።

በንግድ ሳምንት ኤክስፖው ላይ አትክልት እና ፍራፍን ጨምሮ የግብርና ምርቶች እንዲሁም የተለያዩ የሃገር ውስጥ ምርቶች ይቀርቡበታል፡፡

ምርቶቹም ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉና ዋጋቸውም ከመደበኛው የገበያ ዋጋ እንደሚቀንስም ተነግሯል፡፡

በኤክስፖው ላይ የአዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ ከመላው የሀገሪቱ አካባቢዎች የተውጣጡ 168 የንግድ ድርጅቶች እንደሚሳተፉም ሚኒስትር ዴኤታው አስታውቀዋል።

በፂዮን ማሞ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review