የማዳበሪያ ፋብሪካው ኢትዮጵያ በከፍተኛ ወጪ የምታስገባውን ማዳበሪያ በማስቀረት የውጭ ምንዛሪን ለማዳን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ተገለፀ

You are currently viewing የማዳበሪያ ፋብሪካው ኢትዮጵያ በከፍተኛ ወጪ የምታስገባውን ማዳበሪያ በማስቀረት የውጭ ምንዛሪን ለማዳን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ተገለፀ

AMN – ነሐሴ 22/2017 ዓ.ም

የማዳበሪያ ፋብሪካው ኢትዮጵያ በከፍተኛ ወጪ የምታስገባውን ማዳበሪያ በማስቀረት የውጭ ምንዛሪን ለማዳን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ገለፁ።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና ዳንጎቴ ግሩፕ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር ለሚገነባው የማዳበሪያ ፋብሪካ ፕሮጀክት ግንባታ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ የግንባታ ስምምነቱ የግብርናውን ዘርፍ ለመደገፍ አይተኬ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።

እንዲሁም ኢትዮጵያ በከፍተኛ ወጪ የምታስገባውን ማዳበሪያ በማስቀረት የውጭ ምንዛሪን ለማዳን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል ብለዋል።

የግብርና፣ የኢንዱስትሪና የማዕድን ዘርፍ ልማትን በማገዝ በኩል የጎላ አስተዋፅኦ እንደሚኖረውም ነው መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገት በማፋጠን፣ ለስራ ዕድል ፈጠራና ፋብሪካው በሚገነባበት አካባቢ ያለውን ልማት ለማነቃቃት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

ስምምነቱ ለኢትዮጵያዊያን የአዲስ ዓመት ዋዜማ ብስራት ነው ሲሉ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በቅርቡ እንደሚመረቅ የጠቀሱት ሚኒስትሩ፤ የማዳበሪያ ፋብሪካው ሌላኛው ታላቁ ህዳሴ ተደርጎ እንደሚወሰድ ነው የተናገሩት።

ፋብሪካው ኢትዮጵያን በቀጣናዊ የማዳበሪያ አቅርቦት ማዕከል የሚያደርጋት እንደሆነም ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review