በጃፓን ቶኪዮ በሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለሚካፈለው ልዑክ ሽኝት እየተደረገለት ነው

You are currently viewing በጃፓን ቶኪዮ በሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለሚካፈለው ልዑክ ሽኝት እየተደረገለት ነው

AMN-ጳጉሜ 1/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቶክዮ ለሚካፈለው የአትሌቲክስ ልዑክ በስካይ ላይት ሆቴል ሽኝት እያደረገ ይገኛል።

በመርሃግብሩ ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካን ጨምሮ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ አባላት ፣ አትሌቶች እንዲሁም አሰልጣኞች ተገኝተዋል።

ከመስከረም 3 እስከ 11 ለሚካሄደው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና 36 አትሌቶች እና 12 አሰጣኞችን ጨምሮ አጠቃላይ 65 የልዑክ ቡድን አባላት ወደ ስፍራው ያቀናሉ።

በዮናስ ሞላ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review