ማርቲን ዙብሜንዲ ሁለት ግብ ባስቆጠረበት ጨዋታ አርሰናል ኖቲንግሃምን አሸነፈ

You are currently viewing ማርቲን ዙብሜንዲ ሁለት ግብ ባስቆጠረበት ጨዋታ አርሰናል ኖቲንግሃምን አሸነፈ

AMN-መስከረም 03/2018 ዓ.ም

በአራተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በሜዳው ኤምሬትስ ኖቲንግሃምን ያስተናገደው አርሰናል 3ለ0 አሸንፏል።

ለመድፈኞቹ ስፔናዊው አማካይ ማርቲን ዙብሜንዲ ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል።

አጥቂው ቪክቶር ዮኬሬሽ ሌላኛውን ግብ ከመረብ አሳርፏል። ስዊድናዊው አጥቂ በሊጉ ያስቆጠራቸውን ግቦች ሦስት አድርሷል።

ኖቲንግሃም ፎረስትን እየመሩ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ያደረጉት የቀድሞ የቶተንሃም አሰልጣኝ አንጅ ፖስቴኮግሉ አዲሱ ስራቸውን በሽንፈት ጀምረዋል።

በጨዋታው በአርሰናል በኩል ማርቲን ኦዴጋርድ ጉዳት ገጥሞት በኢታን ዋኔሪ ተቀይሮ ወጥቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review