የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ መመረቁን አስመልክቶ በመስቀል አደባባይ ለሚደረገው የድጋፍ ሰልፍ በዋዜማው የማርቺንግ ባንድ የሙዚቃ ትርኢት በከተማዋ በተመረጡ ቦታዎች ላይ ተካሄደ።
የህዝቦች የአንድነት መገለጫ የሆነውን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ምረቃን በማስመልከት ነገ መስከረም 4 ቀን 2018 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ ለሚደረገው የድጋፍ ሠልፍ ቅድመ የጸጥታ ስራ ልምምድ እና የማርቺንግ ባንድ የሙዚቃ ትርኢት ተደርጓል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ዣንጥራር አባይ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው እንዲሁም የአስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ከጸጥታ ቅድመ ጥንቃቄ ልምምድ ባሻገር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ፣ የፌደራል ፖሊስና የአዲስ አበባ ፖሊስ የማርቺንግ ባንድ አባላት የጋራ የአደባባይ ላይ የሙዚቃ ትርኢት አቅርበዋል።
የየተቋማቱ የማርቺንግ ባንድ አባላት በከተማው በተመረጡ 12 ቦታዎች ላይ በመዘዋወር ነው ልዩ ልዩ ሀገራዊ ጣዕመ ዜማዎችን ማሰማታቸዉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በላከዉ መረጃ አስታዉቋል።