አርሰናል አትሌቲክ ቢልባኦን 2ለ0 አሸነፈ

You are currently viewing አርሰናል አትሌቲክ ቢልባኦን 2ለ0 አሸነፈ

AMN-መስከረም 06/2018 ዓ.ም

አርሰናል የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ በድል ተወጥቷል።በኤስታዲዮ ሳንማሜስ አትሌቲክ ቢልባኦን የገጠመው አርሰናል 2ለ0 አሸንፏል።

ኤቤሬቼ ኤዜን ቀይሮ የገባው ጋብርኤል ማርቲኔሊ እና በዮኬሬሽ ተቀይሮ የገባው ሊአንድሮ ትሮሳርድ የመድፈኞቹን ሁለት ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል። በሌላ ጨዋታ በሜዳው ኡኑዮን ሴንት ጂልዋስን የገጠመው ፒ ኤስ ቪ አይንዶቨን 3ለ1 ተሸንፏል። ምሽት 4 ሰዓት ላይ አራት ጨዋታዎች ይከናወናሉ።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review