‎ኢትዮጵያ መውጫ እና መግቢያ በሯን የማበጀቷ ጉዳይ አይቀሬ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ

You are currently viewing ‎ኢትዮጵያ መውጫ እና መግቢያ በሯን የማበጀቷ ጉዳይ አይቀሬ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ

AMN – መስከረም 7/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ መውጫ እና መግቢያ በሯን የማበጀቷ ጉዳይ አይቀሬ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በመደመር እሳቤ የጻፉት 4ኛው መጽሃፍ ”የመደመር መንግሥት” ተመርቆ ለንባብ በቅቷል።

በመፅሐፍ ምርቃቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ ከዘጋት በር እና ደሀ ካስባላት መጠሪያዋ በዓለም ህግ መሰረት እና በሰላም መገላገል አለባት ብለን ስለምናምን በየትኛውም መድረክ ከኢትዮጵያ ጋር በሰላማዊ መንገድ መነጋገር የሚፈቅድ አካ ካለ እጃችን ከምንጊዜውም በላይ የተዘረጋ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሰላምን ታስቀድማለች፣ ድህነትን ትፋለማለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መውጫ እና መግቢያ በሯን የማበጀቷ ጉዳይ አይቀሬ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የጂኦፍራፊ እስረኛ ሆና ለዘላለም ትኖራለች ብሎ የሚያስብ ኢትዮጵያዊ ካለ እርሱ የሞተ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስተሩ፤ ወንድም እህቶቻችንም የኢትዮጵያ የባህር በር አይቀሬ ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበው በፈጠነ ጊዜ እራሳቸውን ለድርድር ዝግጁ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረውም፤ ይህ ጉዳይ ሲሳካ እኛ ላንኖር ብንችልም ልጆቻችን በተዘጋ ሀገር ውስጥ የሚኖሩ ድሃ ሳይሆኑ የታሪክ ሰሪ ልጆች ሆነው ከራሳቸው አልፈው ሌሎች ሀገራትን የሚያግዙ ይሆናሉ ብለዋል፡፡

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review