‎የመሥቀልና የኢሬቻ በዓላት ባህላዊ እሴታቸውን ጠብቀው እንዲከናወኑ ለማስቻል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሠራታቸዉ ተገለጸ

You are currently viewing ‎የመሥቀልና የኢሬቻ በዓላት ባህላዊ እሴታቸውን ጠብቀው እንዲከናወኑ ለማስቻል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሠራታቸዉ ተገለጸ

AMN – መስከረም 7/2018 ዓ.ም

የህዝብ ለህዝብ ትስስር የሚጠናከርባቸዉ እና ለሀገር ገፅታ ግንባታ ትልቅ ፋይዳ ያላቸው የመሥቀል እና የኢሬቻ በዓላት ባህላዊ እሴታቸውን ጠብቀው እንዲከናወኑ ለማስቻል በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሠራታቸዉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ገለፁ፡፡

ቢሮዉ፣ በመስከረም ወር የሚከበሩት እነዚህ የአደባባይ ክብረ በዓላት ባህላዊ እሴታቸውን ጠብቀው በሚከበሩበት ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል።

የቢሮ ሀላፊዋ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት፤ የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት ባህላዊ እሴታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ የሚያስችል በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሠራታቸውን ተናግረዋል።

ሁለቱ በዓላት የህዝብ ለህዝብ ትስስር የሚጠናከርባቸው እና ለሀገር ገፅታ ግንባታ ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ ባህላዊ እሴታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ የጋራ ርብርብ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈሪ በበኩላቸው፣ ይህ ወቅት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ ሌሎችም በርካታ ፕሮጀክቶች የተመረቁበት መሆኑን አስታውሰው፣ በዓላቱ በርካታ ህዝብ የሚታደምባቸው በመሆናቸው የሁላችንም የጋራ ርብርብ እና ጥረት ይጠይቃል ብለዋል፡፡

በፀጋ ታደሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review