ኤብሬቺ ኤዜ የመጀመሪያ ግቡን ባስቆጠረበት ጨዋታ አርሰናል ፖርት ቬልን አሸነፈ

You are currently viewing ኤብሬቺ ኤዜ የመጀመሪያ ግቡን ባስቆጠረበት ጨዋታ አርሰናል ፖርት ቬልን አሸነፈ

AMN-መስከረም 15/2018 ዓ.ም

በእንግሊዝ የካራባኦ ካፕ ሦስተኛ ዙር ጨዋታዎች ማንችስተር ሲቲ ፣ ኒውካስትል ዩናይትድ ፣ ቶተንሃም ሆትስፐርስ እና አርሰናል ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል።

ከሜዳው ውጪ ሀደርስፊልድ ታውንን የገጠመው ማንችስተር ሲቲ 2ለ0 አሸንፏል። ፊል ፎደን እና ሳቪንሆ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ አሳርፈዋል። በሴንት ጀምስ ፓርክ ብራድፎርድ ሲቲን ያስተናገደው ኒውካስትል 4ለ1 ማሸነፍ ችሏል።

ለኤዲ ሀው ቡድን ጆሊንተን እና ዊሊያም ኦሱላ ሁለት ሁለት ግቦችን አስቆጥረዋል። በሌላ ጨዋታ ቶተንሃም ሆትስፐርስ በሜዳው ዶንካስተር ሮቨርስን 3ለ0 ረቷል።

ፓልሂንሃ ፣ ብሬናን ጆንሰን እንዲሁም ጄይ ማክግራዝ በራሱ ላይ ያስቆጠሯቸው ግቦች የሰሜን ለንደኑን ክለብ አሸናፊ አድርገዋል።

ኤብሬቺ ኤዜ የመጀመሪያ ግቡን ባስቆጠረበት ጨዋታ አርሰናል ፖርት ቬልን አሸንፏል። መድፈኞቹ 2ለ0 ባሸነፉበት ጨዋታ ከኤዜ በተጨማሪ ሊአንድሮ ትሮሳርድ ሌላኛውን ግብ በስሙ አስመዝግቧል።

በጨዋታው አማካዩ ክሪስቲያን ኖርጋርድ ለአርሰናል የመጀመሪያ የፉክክር ጨዋታውን አድርጓል። አርሰናል በአራተኛ ዙር ብራይተንን በኤምሬትስ ይገጥማል።

ወልቭስ ከ ቼልሲ ፣ ኒውካስትል ከ ቶተንሃም እንዲሁም ሊቨርፑል ከ ክሪስታል ፓላስ ሌሎች የአራተኛ ዙር ተጠባቂ ጨዋታዎች ናቸው።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review