ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መጪዎቹ ታላላቅ የአደባባይ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ሁሉም የፀጥታ ተቋማት በቴክኖሎጂ ጭምር የታገዘ የተሟላ ዝግጅት ማድረጋቸዉን ገለጹ

You are currently viewing ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መጪዎቹ ታላላቅ የአደባባይ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ሁሉም የፀጥታ ተቋማት በቴክኖሎጂ ጭምር የታገዘ የተሟላ ዝግጅት ማድረጋቸዉን ገለጹ

AMN መስከረም 15/2018 ዓ.ም

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ መጪዎቹ ታላላቅ የአደባባይ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ሁሉም የፀጥታ ተቋማት በቴክኖሎጂ ጭምር የታገዘ የተሟላ ዝግጅት ማድረጋቸዉን ገለጹ፡፡

አቶ ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት በመስከረም ወር በሚከበሩ በዓላት ዙሪያ ከፌደራል፣ ከአዲስ አበባ እና ከኦሮሚያ ክልል የፀጥታ አመራሮች ጋር ውይይት አካሂደናል ብለዋል፡፡

በያዝነው ወር የሚከበሩት የመስቀል ደመራ፣ የኢሬቻ እና ሌሎች የሕዝብና የአደባባይ በዓላት በተሳካ ሁኔታ እንዲከበሩና በሰላም እንዲጠናቀቁ የተደረጉ ዝግጅቶችን ገምግመናል ብለዋል፡፡

ከዚህ በፊት የተከናወኑ የበዓል አከባበሮች የፀጥታ አካላት እና ሕዝቡ በጋራ በመሆን በቅንጅት በመስራታቸው ስኬታማና ለመጪዎቹ በዓላት አከባበር ልምድ የተገኘበት መሆኑን ተመልክተናል።

መጪዎቹ ታላላቅ የአደባባይ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ሁሉም የፀጥታ ተቋማት በቴክኖሎጂ ጭምር የታገዘ የተሟላ ዝግጅት አድርገዋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በዓላቱ ያለምንም የፀጥታ ስጋት ተጀምረው በድምቀት እንዲጠናቀቁ የፀጥታ አመራሩና አባላት ከሕብረተሰቡ ጋር በቅንጅት እንዲሰሩ አቅጣጫ አስቀምጠናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review