የ2018 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል ሃይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀ መንገድ በስኬት ተከብሮ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ

You are currently viewing የ2018 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል ሃይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀ መንገድ በስኬት ተከብሮ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ

AMN – መስከረም 16/2018 ዓ.ም

አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በመላው ሃገሪቱ የተከበረው የ2018 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል ሃይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀ መንገድ በስኬት ተከብሮ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት ኃይሎች ጋር በመቀናጀት በመላው ሃገሪቱ በቴክኖሎጂ የታገዘ በርካታ የፖሊስ ሠራዊት በማሰማራት፤ ከህዝብ፣ ከሃይማኖት መሪዎች፣ ከበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴዎችና ከወጣቶች ጋር ተባብሮ በመስራቱ በሁሉም የሃገሪቱ አካባቢዎች በዓሉ ሃይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀ መንገድ በስኬት ተከብሮ መጠናቀቁን ኤ ኤም ኤን በላከው መረጃ አስታውቋል፡፡

በዓሉ ስኬት እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረገው የሃገሪቱ ህዝብ እንዲሁም ለሀይማኖት መሪዎች፣ ለበዓሉ አስተባባሪ ኮሚቴዎች፣ ለወጣቶች እና በተለይ የተሰጣቸውን ግዳጅ በሚገባ ለተወጡት ለመላው የሃገሪቱ የፀጥታና ደኅንነት ኃይሎች የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ምስጋና አቅርቧል፡፡

ህብረተሰቡ የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ እያሳየ ያለውን ቀና ትብብር በቀጣይ በሚከበሩት የሆራ ፊንፊኔ እና የሆረ አርሰዲ የኢሬቻ በዓላት ላይም በተመሳሳይ አጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ መልእክት አስተላልፏል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review