የጀግኖች ማዕከል ሊገነባ ስለመሆኑ ኮሚሽነር ዘላለም መንግሥቴ (ዶ/ር) ገለጹ

You are currently viewing የጀግኖች ማዕከል ሊገነባ ስለመሆኑ ኮሚሽነር ዘላለም መንግሥቴ (ዶ/ር) ገለጹ

AMN – መስከረም 18/2018 ዓ.ም

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የጀግኖች ማዕከል ግንባታን በደብረ ብርሃን ከተማ አስጀምሯል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዘላለም መንግሥቴ (ዶ/ር)፤ የፖሊስን ዋጋ እና ክብር የሚመጥን ማዕከል እንደሚገነባ ገልጸዋል።

ኮሚሽነሩ ለማኅበረሰቡ ሲል ዋጋ የከፈሉ የፖሊስ አባላት ተገቢውን እንክብካቤ እንዲያገኙ እና እንዲቋቋሙ የሚያስችል ማዕከል የሚገነባ ስለመሆኑም አንስተዋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት በበኩላቸው፣ የማዕከሉ ግንባታ እንዲፋጠን አስፈላጊውን መሠረተ ልማት በማሟላት ከተማ አስተዳደሩ ኀላፊነቱን ይወጣል ብለዋል።

ለከተማው ልማት እና ለሀገር እድገት የፖሊስ ሚና ከፍተኛ ነው ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው፣ ይህንን ውለታቸውን በአግባቡ መክፈል እንደሚገባም አንስተዋል፡፡

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የአማራ ክልል አመራሮች፣ የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር እና የሰሜን ሸዋ ዞን የስራ ኀላፊዎች መገኘታውን የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review