ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ሳምንት የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ተግባራዊ ማድረግ ትጀምራለች

You are currently viewing ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ሳምንት የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ተግባራዊ ማድረግ ትጀምራለች

AMN መስከረም 19/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ሳምንት የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ተግባራዊ ማድረግ እንደምትጀምር የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራ ከንግድ ቀጣናነት ባለፈ የአፍሪካ ዘላቂ ዕድገትና ብልፅግና ለማረጋገጥ ወሳኝ እንደሆነ ይታመናል።

የንግድ ቀጣና ስምምነቱ አፍሪካዊያንን የኢኮኖሚ በማስተሳሰር ፈጣንና ወደ ብልፅግና የሚያሻግር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ማረጋገጥ ያስችላል።

የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 እና የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ድህነትን ለመቀነስ ወሳኝ እንደሆነም ይገለጻል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ለዓለም የንግድ ድርጅት አባልነት በስዊዘርላንድ ጄኔቫ የተደረገውን ስድስተኛ ዙር የሥራ ቡድን ስብሰባ በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

ሚኒስትሩ በመግለጫቸው የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናን መጀመር የሚያስችል የሰነድ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን ተናግረዋል።

በዚህም ኢትዮጵያ በመጭው ሳምንት የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ በይፋ እንደምትጀምር ማስታወቃቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review