በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ውጤቶች እየተመዘገቡባቸው መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ

You are currently viewing በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ውጤቶች እየተመዘገቡባቸው መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ

AMN – መስከረም 22/2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሶማሌ ክልል እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸውም የጅግጅጋ ከተማን የኮሪደር ልማት ስራ እንዲሁም የገበታ ለሀገር ፕሪጀክት አካል የሆነዉን ሸበሌ ሪዞርትን ተመልክተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፣ የጅግጅጋ ከተማ የኮሪደር ልማት ስራ የከተማዋን ገጽታ በአጭር ጊዜ ውስጥ በእጅጉ እንደቀየረው ተናግረዋል።

ይህም ጭስ አልባው ኢንዱስትሪ ተብሎ የሚጠራውን ቱሪዝም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለማስፋፋት የተጀመረውን ስራ ያጠናክረዋል ነው ያሉት።

የገበታ ለሀገር ሸበሌ ሪዞርትም ከኢትዮጵያ ባለፈ ለአካባቢው ጎረቤት ሀገራት ጭምር አገልግሎት የመስጠት አቅም እንዳለውም ጠቁመዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ ታላላቅ ውጤቶች እየተመዘገቡባቸው መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

በከተማ ልማት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችም ኢትዮጵያን የአፍሪካ ምሳሌ እያደረጋት መሆኑንም ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ በስንዴ ልማት ባከናወናቸው ስራ እውቅና ከዚህ ቀደም ዓለም አቀፍ እውቅና ማግኘቷን አንስተው፣ አሁን ደግሞ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ባስመዘገበችው ስኬት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቋም እውቅና እንደተሰጣትም ተናግረዋል።

በሔለን ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review