በግዙፉ ዓባይ ላይ የተገነባው ባለግርማው ድልድይ ለባህርዳር ከድልድይም በላይ መለያ ቀለሟ፣ የቱሪዝም መዳረሻዋ መሆኑን ተመልክተናል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ

You are currently viewing በግዙፉ ዓባይ ላይ የተገነባው ባለግርማው ድልድይ ለባህርዳር ከድልድይም በላይ መለያ ቀለሟ፣ የቱሪዝም መዳረሻዋ መሆኑን ተመልክተናል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ

AMN – መስከረም 26/2018 ዓ.ም

በግዙፉ ዓባይ ላይ የተገነባው ባለግርማው ድልድይ ለባህርዳር ከድልድይም በላይ መለያ ቀለሟ፣ የቱሪዝም መዳረሻዋ መሆኑን ተመልክተናል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ ባህርዳር እንደ መስከረም ንጋት ውበት፣ ተስፋ እና ልማት ሆኖላት ተመልክተናል ብለዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሃ ከነውበት እና ስክነቱ፤ መልክዓ ምድር ከነ ለምነቱ፤ ልምላሜ ከነ ንጹህነቱ የታደለችው የውበት ምልክቷ ባህርዳር በጠንካራ አመራርና ነዋሪዎች የጋራ ጥረት ውበቷ ይበልጥ እየፈካ እና እየደመቀች ነው ብለዋል።

በግዙፉ ዓባይ ላይ የተገነባው ባለግርማው ድልድይ ለባህርዳር ከድልድይም በላይ መለያ ቀለሟ፣ የቱሪዝም መዳረሻዋ መሆኑን ተመልክተናል ብለዋል።

ባህርዳር ውበቷን እና ክብሯን የሚመጥኑ የመናፈሻ ስፍራዎች እየተገነቡ፤ የኮሪደር ልማቱም ከውበት የተሻገረ ልማት አሳላጭ ሆኖ በፍጥነት እና ፈጠራ እሴቶች እያማረች ስለመሆኑም ጠቅሰዋል፡፡

የብልጽግና ጉዟችን መዳረሻም እንደሃገር ወደሚመጥነን ከፍታ መሸጋገር ነው በማለትም አስፍረዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review