የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከቆጣሪ ምርመራ አሠራር ጋር በተገናኘ ዘመናዊ መተግበሪያ ከጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ እንደሚያዉል አስታወቀ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከቆጣሪ ምርመራ አሠራር ጋር በተገናኘ ዘመናዊ መተግበሪያ ከጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ እንደሚያዉል አስታወቀ

AMN መስከረም 30/2018

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቆጣሪ ምርመራ አሠራር ላይ ግልፅነት ተጠያቂነት እና ተአማኒነትን ለመፍጠር የሚያስችል ዘመናዊ መተግበሪያ (Software application) ከጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ እንደሚያዉል አስታዉቋል፡፡

መተግበሪያው ከፍጆታ ክፍያ እና ከኢነርጂ ብክነት ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመቀነስ ብሎም በቆጣሪ ምርመራ ወቅት ለደንበኞች ግልፅነት እና ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ አሠራርን መፍጠር የሚያስችል ዘመናዊ የቆጣሪ ምርመራ ስራ መረጃዎችን በሲስተም መመዝገብ የሚያስችል መሆኑን ጠቁሟል፡፡

ተቋሙ ያበለፀገው ዘመናዊ የቆጣሪ ምርመራን የሚያግዝ አፕሊኬሽን ወደ ሥራ ሲገባ ከዚህ በፊት በማኑዋል ይመዘገብ በነበረው መረጃ ላይ የሚስተዋሉ የምርመራ መረጃ ክፍተቶች በማስቀረት ሲስተም ላይ የተመዘገበውን መረጃ በአንድ ጊዜ ማንኛውም በየደረጃው የሚመለከተው እና ሥልጣኑ የተሰጠው አካል መረጃውን መመልከት የሚያስችል በመሆኑ የሚከናወኑ የቆጣሪ ምርመራ ሥራዎች ላይ የመረጃ አያያዝ ጥራትን እንደሚጨምር አገልግሎቱ ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡

የቆጣሪ መመርመሪያ አፕሊኬሽኑ በቀላሉ ስልክ ላይ በመጫን የቆጣሪ ምርመራ መረጃዎችን ለመመዝገብ የሚያስችል ነው። ይህ አፕሊኬሽን ለሁሉም የቆጣሪ ዐይነቶች ሥራ ላይ ማዋል የሚያስችል ከመሆኑም በላይ በቆጣሪ ላይ የሚደረጉ ሕገ ወጥ ተግባራትን ጨምሮ የቆጣሪ መረጃዎችን ይመዘግባል ተብሏል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review