የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በየአካባቢያቸው የሚያዘወትሯቸውን ባህላዊ ምግቦች ለማስተዋወቅ ያለመ ፌስቲቫል ተከፍቷል።
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከ”ኩሪፍቱ አፍሪካን ቪሌጅ” ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የባህላዊ ምግቦች ፌስቲቫል ሸገር ከተማ በሚገኘው “ኩሪፍቱ አፍሪካን ቪሌጅ” እየተካሄደ ነው።
ከ34 በላይ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችን ባህላዊ ምግቦች የያዘው ፌስቲቫሉ፤ የየአካባቢዎቹን ባህላዊ ምግቦች ማስተዋወቅና በኢትዮጵያዊያን መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከርን ዓላማ ያደረገ እንደሆነም ተገልጿል።
በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የሸገር ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ተሾመ አዱኛ፣ የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ፣ የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እንደገና አበበ እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
በ- በላይሁን ፍስሃ