ትናንት ምሽት በአፉር ክልል ባራህሌ በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ጉዳት ደርሷል

You are currently viewing ትናንት ምሽት በአፉር ክልል ባራህሌ በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ጉዳት ደርሷል

AMN – ጥቅምት 2/ 2018

በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የክልባቲ ራሱ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች ከትናንት ጀምሮ ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ አጋጥሞታል።

በክልባቲ ራሱ ዞን የበራህሌ ወራዳ አስተዳዳሪ አቶ አሊ ሁሴን ለኤኤምኤን እንዳሉት በመሬት መንቀጥቀጡ አንድ የ12 አመት ህጻን ሲሞት ሌሎች 6 ሰዎች ቆስለዋል ብለዋል።

በአደጋዉ በተለይ በቡሬ እና አስ ጉቢ አላ ቀበሌዎች በንብረትና በሰው ላይ ጉዳት ማድረሱንም ተናግረዋል።

ተጎጂዎቹ ወደ ጤና ተቋማት እየተወሰዱ ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም ተናግረዋል።

በመሀመድ ማአር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review