3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤን በአድዋ ድል መታሰቢያ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
ጉባኤዉን በይፋ ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በመጠናቀቁና ግዙፍ ሃገራዊ ፕሮጅክቶች በመጀመራቸዉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር “ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ!” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘዉን 18ኛዉን የሰንደቅ አላማ ቀንን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
በ-ወንድማገኝ አሰፋ