በአንድ አመት ተኩል ጊዜ ውስጥ 35ሺህ ተሽከርካሪዎችን በአንድ ጊዜ ማቆም የሚስችል የመኪና ማቆሚያዎች ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።
ከንቲባዋ ይህንን የገለፁት 3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤው ላይ ነው፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት ለማሳለጥ የሚያስፈልጉ መሰረታዊ ጉዳዮች ውስጥ የፖርኪንግ ልማትን ያነሱ ሲሆን፤ በአንድ አመት ተኩል ጊዜ ውስጥ 35ሺህ ተሽከርካሪዎችን በአንድ ጊዜ ማቆም የሚስችል የመኪና ማቆሚያዎች ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል ብለዋል።

በኮሪደር ልማት አንዱ አካል የሆነው የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች በአንድ አመት ተኩል ጊዜ ውስጥ 150 በላይ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ቦታዎች መገንባታቸውና ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ይህ የተሰራው ምንም አይነት የመኪና ማቆሚያ ባልነበረበት ሁኔታ መሆኑን መገንዘብ እንደሚገባ ገልፀው፤ ህዝቡ በፀሀይ፣ በዝናብ፣ በመፀዳጃ አገልግሎት እጦት የሚንገላታበት ሁኔታ እንደነበር አስታውሰዋል።
በሔለን ተስፋዬ