በመዲናዋ ከ2 መቶ በላይ አገልግሎቶች በአንድ ማዕከል እየተሰጡ ናቸው

You are currently viewing በመዲናዋ ከ2 መቶ በላይ አገልግሎቶች በአንድ ማዕከል እየተሰጡ ናቸው

AMN- ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም

3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ተካሂዷል፡፡

በጉባኤው ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ቡዜና አልከድር፣ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የተለያዩ የስራ ሃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው ልዩ ልዩ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምላሽና ማብራሪያም ሰጥተዋል።

በፌደራል ደረጃ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሚያዚያ ወር ላይ መጀመሩን ያነሱት ከንቲባዋ፤ በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ 107 አገልግሎቶች ዲጂታላይዝድ ተደርገዋል ብለዋል።

በአጭር ጊዜ ግንባታው ተጠናቆ ወደ አገልግሎት በገባው የቦሌ አንድ ማዕከል ህንፃም 96 አገልግሎቶች ወደ ዲጂታል መግባታቸውን አንስተዋል።

በመንግስት ደረጃ ከሚሰጡ 1 ሺህ አገልግሎቶች ውሰጥ አሁን ላይ በከተማ ደረጃ 213 አገልግሎቶች ዲጂታላይዝድ መደረጋቸውን ከንቲባ አዳነች ጠቅሰዋል።

ለዚህም 70 በመቶ የሚሆኑት ባለሙያዎች አዲስ ምሩቅ ተማሪዎች ሲሆኑ ተገቢውን ስልጠና እና ፈተና ወስደው ከነባር ሰራተኛ ጋር ተዋህደው እንዲሰሩ በቂ ዝግጅት መደረጉን አንስተዋል።

የአንድ መሶብ አገልግሎት ፈጣን፣ ቀልጣፋና ምቹ አገልግሎትን ለተገልጋዩ ተደራሽ ማድረግ መቻሉንም ተናግረዋል።

በሚካኤል ህሩይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review