የወል ትርክትን፣ ብሔራዊነትን እና ተግባቦትን ለማሳደግ ጉልህ ሚና የሚጫወተውን ኪነ ጥበብ መደገፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

You are currently viewing የወል ትርክትን፣ ብሔራዊነትን እና ተግባቦትን ለማሳደግ ጉልህ ሚና የሚጫወተውን ኪነ ጥበብ መደገፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

AMN – ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም

የወል ትርክትን፣ ብሔራዊነትን እና ተግባቦትን ለማሳደግ ጉልህ ሚና የሚጫወተውን ኪነ ጥበብ መደገፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል፡፡

በጉባኤው ላይ የምክር ቤቱ አባላትም የተለያዩ ጥያቄዎችን እና አስተያይቶችን አንስተዋል፡፡ በምክር ቤቱ አባላት ከተነሱት አስተያየቶችና ጥያቄዎች መካከል ኪነ ጥበብ ለምናባዊ አስተሳሰብና ለፈጠራ ስራ ልህቀት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡

በዚህም መሰረት ከለውጡ በኋላ ለሀገር ማንሰራራት የሚውሉ አንፊ ቴአትር ቤቶች ግንባታ ብሎም እድሳት መካሄዱ በበጎ ተጠቅሷል፡፡ መሰረቱ የማይናወጥ አካታች የወል ትርክት ለመገንባት ብሎም ተራማጅ አስተሳሰብ በማስረጽ፣ ኋላ ቀር አስተሳሰብን በመስበር በኪነ ጥበብ እያዋዙ ጠንካራ ማህበረሰብ ለመፍጠር ከተማ አስተዳደሩ ኪነ ጥበቡን የበለጠ ለማሳደግ ምን አስቧል የሚል ጥያቄ ከምክር ቤት አባላት ተነስቷል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ይህን አስመልክተው በሰጡት ምላሽ፣ በከተማዋ ሰፊ የኪነ ጥበብ ፍላጐት መኖሩን ጠቅሰው፣ በመዲናዋ በዘርፉ የሚሰሩ ስራዎች ለሀገርም ትልቅ ትርጉም ያላቸው በመሆናቸው፣ እንደ ሌሎች የልማት ስራዎች ሁሉ ለኪነ ጥበቡም ሰፊ ትኩረት እንደተሰጠው አብራርተዋል።

ኪነ ጥበብ የወል ትርክትን፣ ብሔራዊነትን እና ተግባቦትን ለማሳደግ ጉልህ ሚና እንደሚጫወት የተናገሩት ከንቲባ አዳነች፣ ይህን መደገፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል። ሲኒማ አምፒር፣ ሜጋ አንፊ ቴአትር፣ ብሔራዊ ቴአትርና ሀገር ፍቅር ዘመናዊ ሆነው ከተሰሩ የኪነ ጥበብ ስፍራዎች መካከል ተጠቃሽ መሆናቸውንም ከንቲባዋ ጠቅሰዋል::

ነባሮቹን ከማደስ በተጨማሪ መጪውን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ እና ተሰጥኦን ወደ ተግባር መቀየር የሚያስችሉ ከ110 በላይ ፕላዛ እና 50 አንፊ ቴአትር መከወኛዎች ተሰርተዋል። ለቴአትር ቤት ግንባታ ወጪን ሳይጨምር ለቴክኖሎጂና ግብአት ከፍተኛ ወጪ የወጣበት ባለ አስራ አራት ወለል ህንፃም ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡

ከቴአትር ባሻገርም የሲኒማ ዘርፉን ሚና ለማሳደግ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈው ባለ 15 ወለል የሰንጋተራ ሲኒማ ኮምፕሌክስ በቅርቡ እንደሚመረቅ ጠቁመው፣ይህም መንግስት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት የሚያሳይ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በሚካኤል ህሩይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review