ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለከተማዋ ብሎም ለሃገሪቱ ዋንኛ አጋር ለሆኑት በየደረጃዉ ለሚገኙ ግብር ከፋዮች ለታማኝነታቸዉ፤ ለግብር ከፋይነታቸዉ እና ለከተማዋ ልማት ላደረጉት አተዋጽኦ ምስጋና አቀረቡ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለከተማዋ ብሎም ለሃገሪቱ ዋንኛ አጋር ለሆኑት በየደረጃዉ ለሚገኙ ግብር ከፋዮች ለታማኝነታቸዉ፤ ለግብር ከፋይነታቸዉ እና ለከተማዋ ልማት ላደረጉት አተዋጽኦ ምስጋና አቀረቡ

AMN – ጥቅምት 06/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለከተማዋ ብሎም ለሃገሪቱ ዋንኛ አጋር ለሆኑት በየደረጃዉ ለሚገኙ ግብር ከፋዮች ለታማኝነታቸዉ፤ ለግብር ከፋይነታቸዉ እና ለከተማዋ ልማት ላደረጉት አተዋጽኦ ምስጋና አቀረቡ፡፡

‎የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “ግብር ለሀገር ክብር” በሚል መሪ ቃል ለታማኝ ግብር ከፋዮች የእውቅናና ሽልማት መርሀ ግብር በአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሔደ ይገኛል።

በዕውቅና መርሀ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣ የመዲናዋ የግብር ከፋዮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመሩን ገልፀዋል።

‎በዚህም የተነሳ ከተማዋ የምትሰበስበው ገቢ ከፍተኛ እድገት እያሳየ መሆኑን የገለፁት ከንቲባዋ፣ ለአብነትም የከተማዋ ገቢ በ2010 በጀት አመት ከነበረበት 33 ቢሊዮን ብር በ2017 በጀት ዓመት ወደ 233 ቢሊዮን ብር ማደጉን ተናግረዋል።

ለከተማዋ ብሎም ለሃገሪቱ ዋንኛ አጋር ለሆኑት በየደረጃዉ ለሚገኙ ግብር ከፋዮች ለታማኝነታቸዉ፤ ለግብር ከፋይነታቸዉ እና ለከተማዋ ልማት ላደረጉት አተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

‎በሔለን ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review