የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ኮሚሽን እና የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ ከፍተኛ አመራሮች እና አባላት በመዲናዋ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
አመራርና አባላቱ በመዲናዋ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን በጎበኙበት ወቅት እንደገለፁት የልማት ስራዎቹ የህዝቡን ተጠቃሚነትና የከተማዋን ሁሉንተናዊ እድገት የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል።
በመዲናዋ የተከናወኑ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎች ለህግ ማስከበር ስራ የላቀ አበርክቶ እያደረጉ መሆኑንም ገልፀዋል።
ጎብኝዎቹ የተሰሩ ስራዎችን የመጠበቅና በቀጣይም የሚከናወኑ ስራዎችን ስኬታማነታቸውን ለማረጋገጥ ይበልጥ በሃላፊነት ስሜት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
በከተማዋ የተከናወኑ የኮሪደር ፣ የወንዝ ዳርቻ እና የመልሶ ማልማት ስራዎች የከተማዋን ውበት ከማጉላት ባለፈ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ መሆናቸውን ገልጸዋል ።
በሁለት ዙር በተካሄደው ጉብኝት ከ2000 በላይ አመራርና አባላት መሳተፋቸዉን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡