ኢትዮጵያ ሰላም፣ ልማት እና የባሕር በር ያስፈልጋታል ሲሉ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ

You are currently viewing ኢትዮጵያ ሰላም፣ ልማት እና የባሕር በር ያስፈልጋታል ሲሉ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ

AMN- ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ሰላም፣ ልማት እና የባሕር በር ያስፈልጋታል ሲሉ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ፡፡

118ኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን “የማትደፈር ሀገር የማይበገር ሠራዊት” በሚል መሪ ሀሳብ ተከብሯል።

በመርሐ-ግብሩም የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ ኢትዮጵያ ሰፊ ሀብት እና ብዙ ህዝብ ያላት ጥንታዊ የስልጣኔ ጠንሳሽ ሀገር እንደሆነች አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያን ከባህር የመግፋት አላማ ዋነኛ ጠንሳሹ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ናቸው ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የባህር በር ጥያቄያችንን እናሳካለን ሲሉም አስረግጠው ተናግረዋል፡፡

የሰራዊቱ አባላትም ለሰላም፣ ለልማት መረጋገጥ የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ለባህር በርም መዘጋጀት አለብን ሲሉ ነው ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ያስገነዘቡት።

የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ እና የተፈጥሮ ጋዝ እና የማዳበሪያ ፋብሪካ መጀመር የሀገር ማንሰራራት ማሳያ እንደሆነም ጠቁመዋል።

በሀገራዊ ስኬቶች ላይ የመከላከያ ሚና የላቀ ነው ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ ለዚህም ለሰራዊቱ ክብር ይገባዋል ብለዋል።

ለእነዚህ የልማት ተግባራት ስኬታማነት ኢትዮጵያ ታላቅ ክብር እና ምስጋና ታቀርባለችም ብለዋል።

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review