በ17 የአፍሪካ ሀገራት የዝንጀሮ ፈንጣጣ በከፍተኛ ደረጃ እየተሰራጨ እንደሚገኘ የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ

You are currently viewing በ17 የአፍሪካ ሀገራት የዝንጀሮ ፈንጣጣ በከፍተኛ ደረጃ እየተሰራጨ እንደሚገኘ የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ
  • Post category:አፍሪካ

AMN – ጥቅምት 23/2018

የአለም ጤና ድርጅት ባለፉት 6 ሳምንታት በአፍሪካ የሚገኘው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ስርጭት እየጨመረ እንደሚገኝ ይፋ አድርጓል።

በነዚህ ሳምንታት ውስጥ 2682 በበሸታው መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን በተጨማሪም የ17 ሰዎች ህልፈት መመዝገቡ ነው የተገለጸው።

በአሁኑ ወቅት በ17 የአፍሪካ ሀገራት የበሽታው የመዛመት ፍጥነት እያደገ እንደሚገኝ ያስታወቀው ድርጅቱ መንግስታት የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል ተለዋዋጭ ፖሊሲዎችን ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

የአለም ጤና ድርጅት በአሁኑ ወቅት ጦርነት እና ተፈጥሯዊ ምክንያቶች በጤና እና በጤና መሰረተ ልማት ላይ በሚያደርሱት ጉዳት እየተፈተነ እንደሚገኘም ተነግሯል።

በዚህ የተነሳ የዝንጀሮ ፈንጣጣን ጨምሮ ሌሎች ወረርሽኞች ሲከሰቱ ፈጣን ምላሽ የመስጠት አቅሙም እየተገደበ እንደሚገኝ ሮይተርስ አስነብቧል።

ከመስከረም 2025 ጀምሮ በ42 ሀገራት ከ3 ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው ሲያዙ 80 በመቶ የሚሆኑት ተጠቂዎች የሚገኙት በአፍሪካ ነው ።

በአሁኑ ወቅት በዴሞክራቲክ ኮንጎ 1189 ፣ በላይቤሪያ 425 ፣ በኬንያ 285 እና በጋና 215 በበሸታው መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች እንደሚገኝ የአለም ጤና ድርጅት ባወጣው ሪፖርት አመላክቷል።

ከነዚህ መካከከል ባለፉት ስድስት ሳምንታት ከፍተኛ ቁጥር በማስመዝገብ ጋና ፣ ላይቤሪያ እና ኬንያ ተጠቃሽ ናቸው ተብሏል።

በዳዊት በሪሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review