ከኮሪደር ልማት ስራዎች ጋር ተያይዞ በተሰሩ የማዘውተሪያ ስፍራዎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ጨምረዋል

You are currently viewing ከኮሪደር ልማት ስራዎች ጋር ተያይዞ በተሰሩ የማዘውተሪያ ስፍራዎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ጨምረዋል

AMN ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም

በመዲናዋ ከተገነቡ የኮሪደር ልማት ስራዎች ጋር ተያይዞ በተሰሩ የማዘውተሪያ ስፍራዎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች መጨመራቸውን የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ገለጸ፡፡

ቢሮው የ2018 ዓም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም ከባለድርሻ አካላት ጋር በገመገመበት ወቅት እንዳመለከተው በሩብ አመቱ በስፖርታዊ ጨዋነት ላይ በተፈጠረ ግንዛቤ የፕሪሚየር ሊጉን ጨዋታ ወደ አዲስ አበባ መመለስ ተችሏል፡፡

የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የ2018 ዓም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸሙን ከባለድርሻ አካላት ጋር ገምግሟል፡፡

በዚህም በከተማዋ ከኮሪደር ልማቱ ጋር ተያይዞ በተሰሩ የማዘውተሪያ ስፍራዎች ክረምትን ጨምሮ የምሽት ጊዜን ጨምሮ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ የሚያስችሉ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ አመልክተዋል፡፡ እነዚህን የማዘውተሪያ ስፍራዎች የሚጠቀሙ ዜጎች ቁጥር በሩብ አመቱ መጨመሩንም ገልጸዋል፡፡

በሩብ አመቱ በስፖርታዊ ጨዋነት ላይ በተፈጠረ ግንዛቤ የፕሪመሚየር ሊጉን ጨዋታዎች ወደ አዲስ አበባ መመለስ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

በመዲናዋ አዲስ አበባ የስፖርቱን ዘርፍ ለማጠናከር በተሰሩ በርካታ ስራዎች ታዳጊዎች ፣ ወጣቶች እና የጤና ቡድኖች ተጠቃሚ መሆናቸውን የግምገማው ተሳታፊዎች አንስተዋል ፡፡

እየጨመረ ከመጣው የማህበረሰቡ ፍላጎት እና መነሳሳት አኳያ ተጨማሪ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንደሚያስፈልጉ እና የተገነቡትም የሚታዳደሩበት መመሪያ እንደሚያስፈልግ ተሳታፊዎቹ አስረድተዋል፡፡

በሰለሞን በቀለ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review