አዲስ አበባ የብልጽግና ተምሳሌት ሆናለች

You are currently viewing አዲስ አበባ የብልጽግና ተምሳሌት ሆናለች

AMN ጥቅምት 29/2018

አዲስ አበባ የብልጽግና ተምሳሌት ሆናለች ሲሉ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አወሉ አብዲ ገለጹ፡፡

የብልፅግና ፓርቲ የ2018 ዓ.ም ዓመታዊ የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና የአባላቱን አቅም በሚገነቡ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በአዳማ ከተማ መሰጠቱ ይታወቃል።

የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አባላት በሀገሪቷ መሰረታዊ የኢኮኖሚ ዘርፎች በግብርና፣ ቱሪዝም፣ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ዘርፎች ላይ ያጠነጠኑ ስልጠናዎችን ወስደዋል፡፡

የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አባላት ዛሬ በአዲስ አበባ የኮሪደር እና የወንዝ ዳር ልማት ስራዎች፣ የቤት ልማት እና አቅርቦት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አወሉ አብዲ በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች የአመራሩን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጡ መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡

በግብርና፤ በቱሪዝም፤ በከተማ ልማትና በኢንዱስትሪ ዘርፍ በመዲናዋ የተሰሩት የልማት ስራዎችም የብልጽግና ማሳያዎች መሆናቸዉን ገልጸዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ የሚያከናዉናቸዉ አጠቃላይ ስራዎች የኢትዮጵያን ብልጽግና የሚያረጋግጡ መሆናቸዉን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አወሉ አብዲ ለኤኤምኤን ተናግረዋል፡፡

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review