AMN- ጥቅምት 30/2018 ዓ.ም
የማየትና የማለም አቅም ምን ያህል ጉልበት እንዳለው በከተማዋ በተሰሩ የልማት ስራዎች አይተናል ሲሉ የፍትሕ ሚንስትር ዴኤታ አቶ ኤርሚያስ የማነብርሀን ገለፁ ።
የብልፅግና ከፍተኛ አመራሮች በመዲናዋ የተሰሩ የልማት ስራዎችን የጎበኙ ሲሆን በጉብኝቱም የተገኙ አመራሮች በከተማ ስለተሰሩ ልማቶች አስተያየታቸውን ለኤ ኤም ኤን ሰጥተዋል።
የመዲናዋን የልማት ስራዎችን የጎበኙት የፍትሕ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኤርሚያስ የማነብርሀን በከተማዋ የተመለከቱት ውበት እንዳስደነቃቸው ገልፀዋል።
በአጠቃላይ ከግዜው አንፃር የማየት እና የማለም አቅም ምን ያህል ጉልበት እንዳለው በከተማዋ በተሰራው ስራ ተመልክተናል ሲሉ ተናግረዋል ።
በከተማዋ የተገነቡትን ዘርፈ ብዙ የልማት ሰራዎች ወደ መሬት እንዲወርዱ የወጠኑ፣ ያሰቡት እና ተግባራዊ እንዲሆኑ ሀላፊነትን የወሰዱ አመራሮችን አመስግነዋል፡፡ ይህ ስራ በስፋት ሲሰራ በሌሎች ሀገሮች የምናያቸው ነገሮች ቅንጦት አይሆኑብንም ብለዋል ።
እስከዛሬ ላለመለወጣችን የፋይናንስ እና የሃብት ችግር ሳይሆን የማየትና የእንችላለን የማለት ክፍተት እንደነበር አስታውሰዋል።
በሔለን ተስፋዬ